የእስላም ማዕዘናት ማለት ሃይማኖቱ የታነጸባቸው የማዕዘን መሠረቶች
ማለት ነው። እነሱም ቀጥሎ በእብኑ ዑመር አማካይነት በተላለፈው ነቢያዊ
ሐዲስ ውስጥ የተመለከቱት አምስት ማዕዘናት ናቸው።
የኢስላም ማዕዘናት ነቢዩ ሙሀመድ እንዲህ ብለዋል፡- ኢስላም የተገነባው በአምስት መሰረቶች ላይ ነው፡፡
1.ሸሃዳ፡-ከአላህ( በስተቀር) በእውነት ሊገዙት የሚገባ ጌታ የለም ብሎ መመስከር ማለት ከርሱ ውጭ በሰማያትም ሆነ በምድር በእውነት የሚያመልኩት አምላክ እንደሌለና ከርሱ ሌላ ያሉ አማልክት ሁሉ የሐሰት አማልክት መሆናቸውን መመስከር ነው፡፡
ነቢዩ ሙሀመድ መልዕክተኛው ናቸው በማለት እምነትን ማረጋገጥ
2. ሶላት፡-(የእስልምና ሁለተኛው መሰረት ነው የእስልምና ምሰሶ እንደሆነም ተረጋግጧል) በቀን አምስት ጊዜ ተደጋግሞ ይፈጸማል፡፡ ማዕዘናቶቿን ፣ደንቦቿን የጠበቀ ሆኖ ልቦናውን ለአላህ ፍፁም በማድረግ መስገድ (በወንጀልና በሰውየው መካከል ግርዶ ይሆናል)፡፡”
3.ዘካት፡-(ከተቀማጭ ሐብት በየዓመቱ ለድሆች መቋቋሚያ ይሆን ዘንድ መስጠት) ማንኛውም ሙስሊም ከወርቅ / 85 ግራም ያለው ከሆነ ከዓመት በኋላ ከመቶ 2.5 ለዘካ ወጪ ማድረግ ይኖርበታል፡፡
ማንኛውም ከወርቅና ከብር ውጭ ያለ ዘካ ወጪ የሚደረግለት ነገር የተገደበ የሆነ መጠን አለው፡፡
4. ሐጅ፡- ወደተቀደሰችው የመካ ከተማ በመጓዝ ለአካለ መጠን የደረሰና አቅም ያለው ማንኛውም ሙስሊም ወደ ተቀደሰው መስጂድ መሄድ የሚችልበት መጓጓዣ ፣ መሄጃና መምጫ የሚሆነው ገንዘብ፣ ቀለብ ካለው መንገዱም ሰላም ከሆነ ሐጅ ማድረግ ግዴታ ይሆንበታል፡፡
5.ሶውም(ጾም)፡- በየዓመቱ የረመዷንን ወር መፆም ፡፡አላህን በማምለክ አላማ ፆመኛ የሆነ ሰው ከኒያ(ከሃሳብ) ጋር ጠዋት ጎህ ከመውጣቱ(ከመቅደዱ) በፊት ጀምሮ ጸሐይ እስክትጠልቅ ድረስ ከምግብ ፣ ከመጠጥና ከግብረ ስጋ ግንኙነት(ከጾታዊ ግንኙነት ) ከሌሎችም ፆምን ከሚያበላሹ ነገሮች ታቅቦ መዋል ፣ራስን ከስጋዊ ፍላጎት ማቀብ ነው፡፡ ” (ቡኻሪና ምስሊም የዘገቡትሐዲስ)